There were 1,489 press releases posted in the last 24 hours and 399,559 in the last 365 days.

የካስማሰ VIP የእራት ግብዣ ዳሰሳ

ከ ጆኒ ዎከር ጋር በ አጋርነት የተዘጋጀው የካስማሰ የ እራት ግብዣ ፥ የኢትዮጵያን የፈጠራ (የጥበብ ዘርፍ) ኢኮኖሚ ማሻሻል የሚቻልባቸው መንገዶችንም ቃኝቷል።

ADDIS ABABA, ETHIOPIA, July 6, 2023/EINPresswire.com/ -- አርብ ዝነኛው ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ካስማሰ ፥ አዲስ አበባ በሚገኘው ሆቶ ሬስቶራንት የእራት ግብዣ በማዘጋጀት ስለወደፊቱ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ እና የፈጠራ ኢኮኖሚ ለመወያየት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተጽእኖ ፈጣሪ የመዝናኛው ዓለም እና የቢዝነስ ሰዎችን አሰባስቧል።

ከጆኒ ዎከር ጋር በመተባበር የተካሄደው የ"ዎከርስ እራት" መርኃ ግብር፣ የኢትዮጵያ ብራንድ አምባሳደር እና በትውልዱ ከፍተኛ ቅቡልነት ያለው የሂፕ ሆፕ አርቲስት ካስማሰ እንዲሁም የክብር እንግዶች የነበሩት ጀምበሩ ደመቀ፣ ወግዳይት፣ ስካት ናቲ፣ ኡኖ፥ ግዳይ እና ሌሎችም እንግዶችን ተካፍለዋል።

“ይህ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸውን ወዳጆችና የኢንዱስትሪ ባልደረቦችን በመሰብሰብ ፥ የባህላችንን ሁኔታ ለመገምገም ፥ የኢትዮጵያን ሙዚቃና ባህል ለማሳደግ መንገዶችን የምንዳስስበት ግሩም አጋጣሚ ነበር” ያለው ካሳማሰ፣ “ኢንቨስትመንትና የባለቤትነት ብዝሃነት ለኢንዱስትሪ እድገት ወሳኝ ነው። እና ይህ መርኃ ግብር የኢትዮጵያን ባህልና መዝናኛ በዚህ አውድ ለመወያየት የሚያስችል ዘዴን ሰጥቷል።” ሲል አክሏል።

በብዝሃ ባህሉ እና ተሰጥኦን በምልአት በመያዙ ምክንያት የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዘግይቶም ቢሆን አስደናቂ እድገት አሳይቷል። እንደ ስታቲስታ ገለጻ፣ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ማሰራጫ ገበያ የሚገኘው ገቢ በ2023 US$4.79M (ከባለፈው ዓመት 28% ሲበልጥ) እና በ2027 ደግሞ US$7.88M ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

“በእርግጥ የዓለም የሙዚቃ ኢኮኖሚ በፍጥነት እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት የሙዚቃው ዘርፍ ላይ መገንባት እና መስራት ትግል ነው። እዚህ ጋር የሙዚቃ መሠረተ ልማትም ለብቻው በቂ አይደለም። እንደማስበው እንደ ሀገር ፥ በሕዝብ ባህል ውስጥ እራሳችንን መረዳት እየጀመርን ነው ፥ ስለሆነም እንደነዚህ ያሉ ዝግጅቶች ትልምን ለመጋራት ፣ ሀሳቦችን ለማንሳት እና በመጨረሻም የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢኮኖሚ ለመጥቀም የሚረዱ ናቸው” ሲል አክሏል ካስማሰ።

የእራት ግብዣው በጥቁር እና በወርቅ ማጌጫ ያጌጠ ሲሆን የሆቶ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሼፍ ዳንኤል ቢ. አስፋው ከኮክቴሎች ጋር ግሩም የሆነ ሜኑ ለታዳሚዎቹ አሰናድቷል። ታዳሚዎችም ከጆኒ ዎከር ጎልድ የሃይቦል ኮክቴሎች በተጨማሪ ጆኒ ዎከር ብሉ ሌብል ተጋብዘዋል።

“በመሰረቱ የጆኒ ዎከር ብራንድ በላቀ ለውጥ ወደ ፊት የመጓዝ እና በአፍሪካ ባህልን በመደገፍ ጉልህ ሚናን የሚያግዝ ነው። “የዋከር እራት” ከአህጉሪቱ የተውጣጡ እጅግ የተዋጣላቸው የባህል ከያኒዎችን እና ፈጣሪዎች ስብስቦች ናቸው። የኢትዮጵያን ባህል በዚህ አይነት ጠቃሚ መንገድ በማገዛችን ኩራት ይሰማናል።" ብለዋል የዋከር ሃውስ የማርኬቲንግ ስራ አስኪያጅ አድሪያን ደ ዌት።

“የዋከር እራት” አርቲስቶችን እና የመዝናኛ ዘርፍ ፈጣሪዎችን ለማሰባሰብ፣ ለመግባባት፣ ለመደገፍ እና እያደገ ያለውን የአህጉሪቱን የባህል ኢኮኖሚ ለማሳደግ በማሰብ በመላው አፍሪካ ዙሪያ እካሄዳል።

ENDS

Lindile Ndwayana
Celebrity Services Africa
+27 725241956
lindile@csa.global